ጥቁር አዝሙድ
Friday, June 14, 2013
Monday, May 27, 2013
Tuesday, January 15, 2013
Sunday, January 13, 2013
Friday, December 21, 2012
Monday, December 17, 2012
ቁርአን ሱረት መርየም 16 - 37
بسم الله الرحمن الرحيم
በመጽሐፉ ውስጥ መርየምንም ከቤተሰቧ ወደ ምሥራቃዊ ስፍራ በተለይች ጊዜ (የሆነውን ታሪኳን) አውሳ፡፡ (16) ከእነሱም መጋረጃን አደረገች፡፡ መንፈሳችንምም (ጂብሪልን) ወደርሷ ላክን፡፡ ለእርሷም ትክክለኛ ሰው ሆኖ ተመሰለላት፡፡ (17) «እኔ ከአንተ በአልረሕማን እጠበቃለሁ፡፡ ጌታህን ፈሪ እንደ ሆንክ (አትቅረበኝ)» አለች፡፡ (18) «እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ» አላት፡፡ (19) «(በጋብቻ) ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል!» አለች፡፡(20) አላት «(ነገሩ) እንደዚህሽ ነው፡፡» ጌታሽ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው፡፡ ለሰዎችም ታምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነው» አለ፤ (ነፋባትም)፡፡ (21) ወዲያውኑም አረገዘችው፡፡ በእርሱም (በሆዷ ይዛው) ወደ ሩቅ ስፍራ ገለል አለች፡፡ (22) ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡ (23) ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት «አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡ (24) «የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ (25) «ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም፡፡ እኔ ለአልረሕማን ዝምታን ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም» በይ፡፡ (26) በእርሱም የተሸከመቺው ሆና ወደ ዘመዶቿ መጣች፡፡ «መርየም ሆይ! ከባድን ነገር በእርግጥ ሠራሽ» አሏት፡፡ (27)«የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡ (28) ወደርሱም ጠቀሰች፡፡ «በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን!» አሉ፡፡ (29) (ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡» (30) «በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል፡፡» (31) «ለእናቴም ታዛዥ (አድርጎኛል)፡፡ ትዕቢተኛ እምቢተኛም አላደረገኝም፡፡ (32) «ሰላምም በእኔ ላይ ነው፡፡ በተወለድሁ ቀን፣ በምሞትበትም ቀን፣ ሕያው ኾኜ በምቀሰቀስበትም ቀን፡፡» (33) ይህ የመርየም ልጅ ዒሳ ነው፡፡ ያ በርሱ የሚጠራጠሩበት እውነተኛ ቃል ነው፡፡ (34) ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባውም፡፡ (ከጉድለት ሁሉ) ጠራ፡፡ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው «ኹን» ነው ወዲያውም ይኾናል፡፡ (35) (ዒሳ አለ) «አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነውና ተገዙት፡፡ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው፡፡» (36)ከመካከላቸውም አሕዛቦቹ በእርሱ ነገር ተለያዩ፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ወዮላቸው፡፡ (37)
ቁርአን ሱረት መርየም 16 - 37
Monday, December 10, 2012
Saturday, November 24, 2012
Monday, August 13, 2012
Sunday, August 12, 2012
Tuesday, July 10, 2012
በሐዲሰል ቁድስ
አሏህ (ሱ.ወ) በሐዲሰል ቁድስ እንዲህ ብሏል
( እኔ የሰው ልጅ እና አጋንንት የሚገርም ዜና አለን። እኔ ፈጥሬው እርሱ ሌላ ያመልካል። እኔ ሲሳይ ሰጥቼው እርሱ ሌላን አካል ያመሰግናል። በጎ ነገሬ ወደባሮቼ ይወርዳል። የነርሱ ክፉ ነገር ወደኔ ይመጣል። እኔ ከነርሱ ምንም ነገር የማልፈልግ ሆኜ እያለ በእዝነቴ የነርሱን ውዴታ ለማግኘት እጥራለሁ። እነርሱ ግን እኔን የሚከጅሉ ሆነው እያለ በሐጢአት ያስቆጡኛል። እኔን የሚያስታውሱ አብረውኝ ናቸው ። ከኔ ጋር መሆን የፈለገ ያውሳኝ ። የሚታዘዘኝን እወዳለሁ። የሚያምጹብኝ ከእዝነቴ ተስፋ እንዲቆርጡ አላደርጋቸውም ። ወደኔ ከቶበቱ ወዳጃቸው ነኝ። እምቢ ካሉም ሐኪማቸው ነኝ። ከነውር ላጸዳቸው በመከራ እፈትናቸዋለሁ። በጎ ስራ ከኔ ዘንድ አስር እና ከዚያ በላይ እጥፍ ምንዳ ያስገኛል። ወንጀልን ግን ራሱን ብቻ እጽፋለሁ። ወይም ይቅር እላለሁ። በክብሬና በልቅናዬ እምላለሁ ፣ ከወንጀል ምህረት ከጠየቁኝ እምራቸዋለሁ። ቶብቶ ወደኔ የመጣን ከሩቅ እቀበለዋለሁ። ከኔ የሸሸን ከቅርብ ሆኜ እጠራዋለሁ። የት ትሄዳለህ ? ከኔ ሌላ አምላክ አለህን ? እለዋለሁ ። )

Wednesday, July 4, 2012
Monday, July 2, 2012
Sunday, July 1, 2012
Friday, June 29, 2012
Thursday, June 28, 2012
Subscribe to:
Posts (Atom)