Tuesday, July 10, 2012

በሐዲሰል ቁድስ

አሏህ (ሱ.ወ) በሐዲሰል ቁድስ እንዲህ ብሏል
( እኔ የሰው ልጅ እና አጋንንት የሚገርም ዜና አለን። እኔ ፈጥሬው እርሱ ሌላ ያመልካል። እኔ ሲሳይ ሰጥቼው እርሱ ሌላን አካል ያመሰግናል። በጎ ነገሬ ወደባሮቼ ይወርዳል። የነርሱ ክፉ ነገር ወደኔ ይመጣል። እኔ ከነርሱ ምንም ነገር የማልፈልግ ሆኜ እያለ በእዝነቴ የነርሱን ውዴታ ለማግኘት እጥራለሁ። እነርሱ ግን እኔን የሚከጅሉ ሆነው እያለ በሐጢአት ያስቆጡኛል። እኔን የሚያስታውሱ አብረውኝ ናቸው ። ከኔ ጋር መሆን የፈለገ ያውሳኝ ። የሚታዘዘኝን እወዳለሁ። የሚያምጹብኝ ከእዝነቴ ተስፋ እንዲቆርጡ አላደርጋቸውም ። ወደኔ ከቶበቱ ወዳጃቸው ነኝ። እምቢ ካሉም ሐኪማቸው ነኝ። ከነውር ላጸዳቸው በመከራ እፈትናቸዋለሁ። በጎ ስራ ከኔ ዘንድ አስር እና ከዚያ በላይ እጥፍ ምንዳ ያስገኛል። ወንጀልን ግን ራሱን ብቻ እጽፋለሁ። ወይም ይቅር እላለሁ። በክብሬና በልቅናዬ እምላለሁ ፣ ከወንጀል ምህረት ከጠየቁኝ እምራቸዋለሁ። ቶብቶ ወደኔ የመጣን ከሩቅ እቀበለዋለሁ። ከኔ የሸሸን ከቅርብ ሆኜ እጠራዋለሁ። የት ትሄዳለህ ? ከኔ ሌላ አምላክ አለህን ? እለዋለሁ ። )

No comments:

Post a Comment